በኢትዮጵያ የሰላም ሂደት ውስጥ በሴቶች ላይ የሚደርስ መገለል ሲፈተሽ፡ የዳራ/የአውድ ጥናት

ይህ የዳራ/አውድ ጥናት ሰነድ የአውሮፓ የሰላም ተቋም በጀርመን ፌዴራላዊ የውጭ ጉዳይ ጽሕፈት ቤት ድጋፍ እየመራው ያለው እንቅፋቶችን ማስወገድ፣ ሰላምን ማበጀት የተሰኘ ፕሮጀክት አካል ነው። ጥናቱ ትኩረት የደረገበት ጉዳይም በኢትዮጵያ ውስጥ በስርዓተ ጾታ እና በግጭት መካከል ያለው መስተጋብር በተለይም በሰላም ግንባታ ጥረቶች ላይ ሴቶች እንዴት እና የት ቦታ የመሪነት ሚና እንደተጫወቱ እንዲሁም ትርጉም ያለው ተሳትፎ እንዳደረጉ መመርመርን ነው። ግኝቶቹም የሴቶችን ተሳትፎ የሚያሳንሱ ለረጅም ጊዜ የቆዩ እንቅፋቶችን አጉልተው የሚያሳዩ ሲሆን፤ ግጭትን በመከላከል እና በሰላም ሂደቶች ውስጥ ሴቶች ያላቸውን ሚና ለማሳደግ የሚጠቅሙ ተጨባጭ እርምጃዎችንም ያቀርባሉ። እነዚህ ሐሳቦች ደግሞ ገና እያደጉ ያሉ አካባቢያዊ የሰላም ግንባታን በመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ ጭምር የሴቶችን ትርጉም ያለው ተሳትፎ ለማሳደግ የሚሆኑ በማስረጃ ላይ የተመሠረቱ ምክረሐሳቦችን ለፖሊሲ አውጪዎች እና ለባለሙያዎች በማስጨበጥ አለም አቀፉን የሴቶች፣ ሰላም እና ደህንነት(WPS) አጀንዳዎች ወደፊት የማስኬድ ግብ ላለው Status Quo or Bold Adaptation? Reclaiming the Women, Peace and Security Agenda (ያለውን ሁኔታ ማስጠበቅ ወይስ ጽኑ ተዋህዶ? የሴቶች ሰላም እና ደህንነት አጀንዳን እንደገና መጠየቅ) ለተሰኘው ዓለም አቀፍ ሪፖርት አስተዋፅኦ ያደርጋሉ።
ከዚህ የዳራ ጥናት ሌላ ሁለት Navigating Barriers To Women’s Participation in Policy Spaces Intersecting with Environmental Peacebuilding (ከአከባብያዊ ሰላም ግንባታ ጋር በሚገናኝ የፖሊሲ ምህዳር ውስጥ ለሴቶች ተሳትፎ እንቅፋት የሆኑትን መቃኝት)እንዲሁም Reclaiming the Women Peace and Security Agenda in Sudan: A Background Paper (በሱዳን የሴቶች ሰላምና ደህንነት አጀንዳን መመለስ: የመሰነዘሪያ ሰነድ)(መሰረታዊ ሰንድ) የሚሉ ርእሶች ያሏቸው ጥናቶች ተዘጋጅተዋል። እነዚህም ጥናቶች Status Quo or Bold Adaptation? Reclaiming the Women, Peace and Security Agenda (ያለውን ሁኔታ ማስጠበቅ ወይስ ጽኑ ተዋህዶ? የሴቶች ሰላም እና ደህንነት አጀንዳን እንደገና መጠየቅ) ለተሰኘው ዓለም አቀፍ ሪፖርት ግኝቶች እንደግብዓት አገልግለዋል።
